smart
smart
smart
smart
smart
smart
smart
smart
"ኢትዮጵያዊነት ትልቅ እምነት ሰዋዊነት ያለበት በፈሪሃ ፈጣሪ የታጠረ እንደ ምንጭ በጠራ ዉስጣዊ ማንነት የተመሰለ በብዝሃነት ልዩነት ግን በአንድ ደማቅ መዓዛና ጣዕም የተዋቀረ ሙሉዕነትና ልዕልና ነዉ፡፡ ዛሬ ላይ ይህን ጣዕም አተን መጥፎ መዓዛን ብንሸትም ከኢትዮጵያዊነት ወተን ተጥለን ነዉና በእኛነታችን እምነት ሁሉን ትተን ይቅር ብለን ወደ ቀደመዉ ዥንጉርጉር አንድነታችን በልጆቻቸን እኛነት ይመለሳል፡፡"
በአንድ አካባቢ የሚኖሩ የሚዋደዱ ባልና ሚስት ነበሩ ታድያ እነዚህ ባልና ሚስት መልካምና ደግ በመሆናችዉ እየደገሱ ደሃዎችን ይመግቡም የይረዱም ሰለነበር ጎረቤታቸዉ በጣም ይቀናም ይጠላችዉማል፡፡ታድያ ሚስትየዉ ታረግዝና ልጅ ሰላልነበራቸዉ ልጅ ሊያገኙ ሰለሆነ በጣም ደሰትኛ ይሆናሉ ግን በድንገት ባልየዉ ይሞታል እናም ይቺ ሴት ብቻዋን ትቀራለች ከቆይታ ቡኋላ ልጁም ይወለድና እንኳን ለሰዉ ለራሷም ምትብላዉ ለጇንም መንክባከብ ያቅታታል በጣም በተቸገረች ግዜም ጎረቤቷጋ ሂዳ ተቸግሪያለውና እባክህ አበድረኝ ብላ ትጠይቀዋለች፡፡ እሱም ያበድራታል ከዛም የተበደረችዉን ከተጠቀመች ቡኋላ ግን መክፈል ያቅታታል ታድያ በዚህ ወቅት ይህ ክፉ ጎረቤት ይህን ጥሩ አጋጣሚ ተጠቅሞ ልጇን ከሷ ነጥቆ በሳጥን አርጎ አርቆ ይጥለዋል፡፡
ከዛም እንዳጋጣሚ በዚያ ጫካ የሚያልፍ አንድ ገበሬ ወደ እርሻዉ ብምሄድ ላይ ሳለ በርቅት አንድ ሳጥን ያያል ከዛም ምን ይሆን ብሎ ያስብና ተጠግቶ ለመክፈትና ለማየት ወሰኖ ወደ ሳጥኑ ይሄዳል፡፡ ከደረሰም ቡኋላ ሳጥኑን ሲከፍተዉ ያልጠበቀዉና ያላሰበዉን የሚያምር ህፃን በሳጥኑ ውስጥ ያያል፡፡ታድያ ይህ ነጋዴ ጥሎት ሊሄድና በዚህ ሊተወው አልፈቀደም እንዲያዉም ልጅ ስላልነበረዉ ይሄ ልጅ የፈጣሪ ስጦታ ነዉ ብሎ እንደ ልጁ ሊያሳድገዉ አስቦ ወደ ቤቱ ይወስደዋል፡፡
ታድያ ከተወሰኑ ጊዜያት ቡኋላ ያ ክፉ ጎረቤት ወደ ሌላ ሃገር ለመሄድ አስቦ መንገድ ይጀምራል ታድያ እየተጓዘ ባለበት ወቅት ልክ የዚያ ገበሬ ቤት አካባቢ ሲደርስ ይመሽበታል ከዛም የመሸበት እንግዳ ነኝ እባክህ በቤትህ አሳድረኝ ብሎ ገበሬዉን ይጠይቀዋል፡፡ገበሬዉም ቤት የፈጣሪ ነዉ ምንችግር አለዉ ግባ ብሎ ካስገባዉ ቡኋላ ስጦታዬን ጠርቶ እግሩን እንዲያጥበዉ ያደርጋል ከዛም እራት እንዲበላ እጁን በዛዉ አሰታጥቦት እራት በላልተዉ ከጨረሱ ቡኋላ እሳት እየሞቁ መጫወት ይጀምራሉ ታድያ በጫወታ መሃል ስለልጁ ይነሳና ይህ ክፉው ጎረቤት ልጅህ ነዉ ብሎ ይጠይቀዋል ገበሬዉም አዎ ብሎ ይመልስለታል ክፉዉም ጎረቤት ይቀጥልና በልጁ ስም ተገርሞ እንዴት ስጦታዬ ልትለዉ ቻልክ ብሎ ሲጠይቀዉ ታሪኩን በሙሉ ያጫዉተዋል፡፡ታድያ በዚህ ሰአት ይህ ክፉዉ ጎረቤት ትዝ ይለዋል ያ የጣለዉ ልጅ ሰጦትዬ መሆኑ ወዲያው ይናደድና ሊያስገድለዉ አስቦ ነጋዴዉን እንዲህ ብሎ ያታልለዋል እኔ በሃገሬ በጣም የተከበርኩና ሀብታም ነኝ በሱ እድሜም የምቶን ሴት ልጅ አለቺኝ እናም ለሷ ከሱ የተሻለ ሌላ ጥሩ ባል አላገኝላትም ከሷ ጋር አብረዉ ይሁኑ ይላመዱ ቤቴንም እስክመለስ በደምብ ያስተዳድርልኝ ብሎ ይለዋል ገበሬዉም ደስ ብሎት በሃሳቡ ይስማማል፡፡
ከዛም ይህ ክፉ ጎረቤት ይሄ ደብዳቤ ይዞ ሚመጣውን ልጅ ገድላቹ አርቃቹ ጣሉት የሚል በወረቀት ላይ ጽፎ በደብዳቤ ዉሰጥ አሽጎ ለማንም እንዳታሳይ አንተም ብቶን ቤት ሰደርስ ለኔ ባለሟሎች ብቻ ስጥቸዉ ብሎ አስጠንቅቆ ምልክት ሰቶት ይሸኘዋል፡፡ ይህም የዋህ ልጅ ደብዳቤዉን ይዞ እየሄደ ሳለ በመንገድ ላይ አንድ አስማት ያላችዉ ትልቅ ሰዉ ያገኙታል ከዛም ምንድነዉ የያዝከዉ ብለዉ ስጦታዬን ይጠይቁታል እሱም ደብዳቤ ነው ይላቸዋል፡፡እሳቸዉም እስኪ ልየዉ ስጠኝ ይሉታል እሱም አይ ለማንም አትስጥ ተብያለዉ ብሎ እምቢ ይላቸዋል ግን እሳቸዉ አስማት ስላላችዉ በውስጡ ምን እንደተፃፈ ያዉቁ ነበር ግን በሱ የዋህነትና ታማኝነት በጣም ተገርመዉ ሊያድኑት ያስቡና ወረቀቱ ላይ በትንፋሻቸው ኡፍፍፍ ብለዉ ደብዳቤዉ ሳይከፈት ጽሁፉን ይቀይሩታል ከዛም በሰላም ግባ ብለዉ ተሰናብተዉት ይሄዳሉ፡፡
እሱም ደብዳቤዉን ይዞ መንገዱን ይቀጥልና ከክፉዉ ጎረቤት ይደርሳል ከዛም ደብዳቤዉን ስጥ ለተባሉት ባለሟል ይሰጣቸዋል ባለሟሉም ደብዳቤዉን ከፍተዉ ሲያነቡ እኔ በጣም ሰለ ምቆይ ይህ ደብዳቤ ይዞ የሚመጣዉን ልጅ ተንከባከቡት እንደኔ ያዘዛቹህንም ታዘዙለት ልጄንም ድል ባለ ድግስ ደግሳቹ አጋቧቸዉ ሀብቴንም አዉርሷቸዉና በደስታ አንድ ላይ ይኑሩ የሚለዉን ካነበቡት ቡኋላ ወዲያዉ ካባ አለበሱት የቤቱ አለቃ ሆነ ለሰርጉም ሽር ጉድ ተጀመረ ከዛም በሃገሩ ታይቶ ማይታወቅ ትልቅ ድግስ ተደገሰ በዚም ድግስ ቀን ይህ ክፉ ጎረቤት ይመጣል ልጁን ገለዉ አርቀዉ ጥለዉልኛል ተገላገልኩ እያለ በሃሳቡ እየተደሰተ ወደ ቤቱ ሲደረስ ትልቅ ድግስ ያያል ከዛም ባካባቢዉ ያሉትን ሲጠይቅ እርሶ ባሉት መሰረት ደብዳቤ ይዞ የመጣዉን ልጅ ሃብቶን አዉርሰን ድል ባለ ድግስ ልጆን እየዳርንለት ነዉ ይሉታል ታዲያ በዚን ግዜ ይህ ክፉ ጎረቤት በድንጋጤ ይሞታል፡፡ልጁም ሃብቱን ወርሶ ሃብታም ሆኖ ካገባት ቆንጆ ሚስቱ ጋ ኑሮዉን በደስታ ቀጠለ ይባላል፡፡
ሁለት የኔ ቢጤ ደሃ ሰዎች ነበሩ ታድያ እነኚህ የኔ ቢጤዎች ከአንድ ሃብታም ቤት ፊትለፊት ይለምኑ ነበር አንደኛዉ ሰራ ብዙ አይወድም ሃብታሙን ሰውዬ ሲገባና ሲወጣ እየጠበቀ እያሞጋገሰዉ እየመረቀው ይለምን ይማፀን ነበር አንደኛዉ ግን ያገኘዉን እየሰራ የተገኘዉን እየበላ ፈጣሪዉን እያመሰገነ ይኖር ስለነበረ ይህ ሃብታሙ ሰዉዬ በጣም ይጠላዉ ነበር ታድያ ለዚያኛዉ እሱን ለሚያሞጋግሰዉ የኔ ቢጤ ተለቅ ያለ ኬክ ደብቆ ይሰጠዋል፡፡ይህ የኔ ቢጤ ታድያ በሰጠዉ ኬክ ይናደዳል እኔ ምፈልገዉ ብር እንጂ ኬክ አይደለም ብሎ ለዛኛዉ የኔቢጤ ይነግረዋል በዚህን ግዜ ፈጣሪዉን እየለመነ ሚኖረዉ የኔቢጤ በቃ አንተ ብር ከሆነ ምትፈልገዉ እኔ እርቦኛል ኬኩን ልግዛህ ይለዋል እሺ ብሎ ተስማምተዉ ይሸጥለታል፡፡
በነጋታዉ ይህ ሃብታም ከቤቱ ሲወጣ የሚያሞጋግሰዉን የኔቢጤ እዛዉ ተቀምጦ ያየዋል ያኛዉ ግን በቦታዉ የለም ነበር ታድያ ቀረብ ይልና ትላንት የሰጠሁህን ኬክ ምን አረከዉ ብሎ ይጠይቀዋል እሱም እኔ ምግብ ሳይሆን በሰአቱ ብር ነበር ምፈልገዉ ስለእዚህ ከኔ ጋር ለነበረዉ የኔቢጤ ሸጥኩለት ብሎ ይመልስለታል፡፡ ከዛም ይህ ሃብታም በነገሩ በጣም እየተገረም ትላንት ኬኩን ስሰጥህ በዉስጡ ብዙ ወርቆችን አርጌ ደብቄ ነበር የሰጠሁህ ግን አየህ አንተ የተሰጠህን ተቀብለህ ስላላመሰገንክ ባለዉ ለሚያመሰግነዉና ሁሌም ፈጣሪን ለሚለምነዉ ለሱ አብዝቶ ሰጠዉ ብሎት እሱም በነገሩ ተምሮ ከዛ ቡኋላ ፈጣሪዉን እየለመነ መኖር ጀመረ ይባላል፡፡
በአንድ አካባቢ የሚኖሩ በጣም ደግና የዋህ ሰዉ ነበር ይህም ሰዉ የተራቡትን ያበላል የተጠሙትን ያጠጣል እንግዳ ተቀብሎ አብልቶ አሳድሮ ስንቅ አስይዞም ይልካቸው ነበር እናም ከእለታት በአንድ ቀን ሶስት ሌቦች ረዥም መንገድ ተጉዘዉ ሲመሻሽ እሱ ቤት አካባቢ ይደርሳሉ ጎራ ብለዉም እንዲያሳድራቸዉ ይማፀኑታል እሱም ደስ ብሎት እሺ ይላቸዉና ወደ ቤቱ ያስገባቸዋል፡፡በቤቱም ሲገቡ በሚያዩት ዕቃና ቁሳቁሶች በጣም ተገርመዉ ሊዘርፉት ያስባሉ ይህም ደግ ሰዉ ግን ምንም አያዉቅምና እነሱን ለማስተናገድ ደፋ ቀና በማለት ዉሃም አምጥቶ የሶስቱንም እግር ያጥባቸዋል እራትም አስቀርቦ ጥግብ ብለዉ እንዲበሉ ካደረገ በኋላ ቡና አስፈልቶ እየተጫወቱ የሆድ የሆዳቸዉን እያወጉ ከጠጡ በኋላ በእርሱ አልጋ እንዲተኙ መኝታዉን ይለቅላቸዋል እነሱ ግን አይሆንም እኛ እዚዉ አንጥፍልንና እዚዉ እንተኛለን አንተ አልጋዉ ላይ ተኛ ይሉታል
እሱ ግን እንግዳ ክቡር ነዉ እኔ አልጋዉ ላይ ተኝቼ እናንተ እዚህ ልትተኙ አይገባም ግዴየለም እናንተ አልጋዉ ላይ ተኙ ብሎ ያሳምናቸዋል እነሱም እሺ ብለዉ ይተኛሉ ታድያ ሁሉም ከተኙና ከጨለም በኋላ ተቀሳቅሰዉ ሰርቀዉት ለመጥፋት እንደ ዕቅዳቸዉ ለማድረግ ይነሳሉ ግን መልካምነቱና ደግነቱ በሃሳባቸዉ መጣባቸዉ ለመስረቅ በጣም ከበዳቸዉ እንዴት ይህን መልካም ሰዉ እንደዚ እናደርጋለን ብለዉ ተነጋገሩ ከዛም በኋላ ለመተዉ ተስማምተዉ ተምልሰዉ ተኙ ሲነጋም ከእርሱ ዘንድ ሄደዉ እኛ ሌቦች ነን ትላንት አንተን ሰርቀንህ ልንሄድ አስበን ነበር ግን ያንተ መልካምነትና ደግነት ካይምሮችን በላይ ሆኖ ይህን ባንተ ላይ ማድረግ ከበደን እናም ይቅርታ አርግልን ለሃሳባችን ከኛ ክፉ ሰራ ያንተ መልካምነት ይበልጣልና ካሁን በኋላም ወደ ስርቆት አንመለስም ሰርተን እንኖራለን ብለዉ ይቅርታ አርጎላቸዉ ስንቅም አስቋጥሮላቸዉ ወደ ሃገራቸዉ ሰደዳቸዉ፡፡
በአንድ የግብፅ ሃይቅ ዉሃ ውስጥ የሚኖር አንድ አዞ ነበር ታድያ ይህ አዞ ከእለታት በአንዱ ቀን በዉሃ ዉስጥ የሚኖሩ አሳዎችን ይመገብና ትናንንሽ ስጋዎች በጥርሶቹ ዉስጥ ገብተዉ ይቀሩበታል። ታድያ በነዚህ ስጋዎች ምክኒያት ጥርሶቹን እየጠዘጠዘው ያመዋል። ከዛም ይህ አዞ በጣም ተጨንቆ ከዉሃ ዉስጥ ይወጣና ቁጭ ሲል ከዉሃው ዳር ባለ አንድ ዛፍ ላይ አንድ ወፍ ይመለከታል ይችንም ወፍ እንዲ ብሎ ይጠይቃታል። በጥርሴ መሃል ትናንሽ ስጋዎች ገብተዉ እያመመኝ ነዉ ምን ይሻለኛል ይላታል እሷም ታድያ የማትበላኝ እና የምንተማመን ከሆነ እኔም በጣም ስለራበኝ ከአፍህ ውስጥ ገብቼ ከጥርሶችህ መሃል እያወጣዉ እበላቸዋል ትለዋለች።
እሱም በሃሳቡ ይስማማና ተማምነዉ ቃል ከተገባቡ በኋላ እሱም አፉን ከፍቶ ቁጭ ይላል እሷም እንዳለቸዉ ከአፉ ውስጥ ገብታ ከጥርሱ መሃል ያሉትን ስጋዎች አንድ በአንድ እያወጣች ትበላቸዋለች ከዛም በልታ ትጨርስና ከአፉ ወታ በራ ከነበረችበት ዛፍ ላይ ታርፋለች።ታድያ እሷም በመጥገቧ እሱም የሚያመዉ ሰለተወው ሁለቱም ተደስተዉ ተመሰጋግነዉ እሷም በረረች እሱም ወደ ዉሃው ገባ ይባላል።
ታድያ ልጆች እነዚህ እንስሣት አያወሩም በባህሪም አይገናኙም ግን ተስማምተዉ እና ተማምነዉ አዞው የጥርሶቸን ንፅህና በመጠበቅ ከሚጠዘጥዘዉ በሽታ ሲጠበቅ ወፏ ደግሞ ምግቧን ከአዞዉ አፍ ውስጥ ታገኛለች። ታድያ ከዚህ ምንማረዉ እርስ በእርስ ተከባብረንና ተቻችለን ከኖርን ሁላችንም አንዳችን ለአንዳችን መዳኒት ሆነን መኖር እንችላለን።
ጉንዳኖች በመንጋ ሲሆን የሚኖሩት በአንድ መንጋ በሺዎች የሚቆጠሩ ጉንዳኖች ይኖራሉ ጉንዳኖች በአንድ ላይ ከሚኖሩ ነፍሳት አንዱ ሲሆኑ በየስራ ድርሻቸዉ ይከፋፈላሉ። ንግስቷ ጉንዳን ስራዋ እንቁላል መጣል ሲሆን ሌሎቹ ሴቶች ጉንዳኖች ደግሞ ሰራተና ሲሆኑ እጩን መመገብ፣ ጎጆዉን ማፅዳት፣ ለምግብ የሚሆኑ ግብዓቶችን መሰብሰብና ማቅረብ፣ ጎጆውን ከሌሎች ነፍሳት መጠበቅ ሲሆን ወንዱ ጉንዳን ግን ስራዉ ንግስቷን ጉንዳን እንቁላል እንድትጥል ማጥቃት ነዉ። ጉንዳኖች የሚያዳምጡበት ምንም አይነት ጆሮ መሰል ህዋስ የላቸዉም ነገርግን እግራቸዉና ጉልበታቸዉ ላይ ነገሮችን የሚያውቁበት የሚገልፁበት ቱቦ አላቸዉ የሚያዳምጡትም በንዝረት ነዉ። በሌላ በኩል ደግሞ በአካላቸዉ ላይ አንቴናዎች እና ፀጉሮች ሲኖራቸዉ ይህ ለምግብነት የሚሆናቸዉን ግባዓቶች የት እንደሚገኙ ለማወቅ ይረዳቸዋል።
ጉንዳኖች ትንንሽ ቢሆኑም ጡንቻቸዉ ግን ከአካላቸዉ አንፃር በጣም ጠንካራ ነዉ ታድያ ይህ ከእነሱ አካል ከ10 እስከ 50 እጥፍ የሚሆን ነገርን የመሸከም አቅም አላቸዉ። እነዚህ ጉንዳኖች ሁለት የሕይወት ወቅት አላቸዉ አንደኛዉ የሚንቀሳቀሱበት ሲሆን በዚህን ጊዜ በየቀኑ ይንቀሳቀሳሉ ይሄዳሉ ምግባቸዉን ይሰበስባሉ ወደ ማታ አካባቢ ልክ እንደ ሰዉ ለነገ ጠዋት ይሆናቸዉ ዘንድ ጊዜያዊ ጎጆ ሰርተዉ ያርፋሉ ከዛም በነጋ ጊዜ ስራቸዉን ይቀጥላሉ ሌላኛዉ ደግሞ በጎጃቸዉ ቁጭ የሚሉበት ሲሆን በዚህ ጊዜ ደግሞ ንግስት ጉንዳን እንቁላል ምትጥልበት እና እስኪፈለፈል ድረስ ያለዉ ወቅት ነዉ። ታድያ ልጆች ከዚህ ምንማረዉ ምንፈልገዉን ለመሆን እና ለማግኘት ጠንክረን መማር እናዳለብን ነዉ